ከሰዎች የምትፈልገውን የትኛውም ነገር ቀድመህ በመስጠት ታገኛለህ
(The Law of Action and Reaction)
ይህ ህግ የድርጊትና የመቀበል ህግ ነው። አንድ ሰው አንድ ነገር ላይ የሚያደርገው ድርጊት ተመልሶ በአድራጊው ላይ ተፅዕኖን ይፈጥራል። አንድን በር በቦክስ ብንሰብረው በሩም እጃችንን መስበሩ ወይም ደግሞ ክፉኛ ማሳሙሙ አይቀርም። አንድን ድንጋይ ገፍተን ለማንቀሳቀስ ስንሞክር ድንጋዩም በተመሳሳይ ሀይል እኛን ወደ ኋላ ይገፈትረናል። አንዳንዴም ከድንጋዩ ገፍታሪ ሀይል አንፃር ሚዛናችንን ስተን ወደኋላ ልንወድቅ አንችላለን። የትኛውም ወደፊት የሚደረግ ሀይል ካረፈበት ነገር ተንፀባርቆ እኛ ላይ ወደ ኋላ ተፅዕኖውን ያሳርፋል። ይህ መሰሉን ክስተት ነው አይዛክ ኒውተን «The law of action and reaction» በማለት የገለፀው። በራሱ ቋንቋም ሲገልፀው «Every action force has an equal and opposite reaction force»።
«የእጁን አገኘ» ይላሉ አበው ሲተርቱ! የስራውን አገኘ እንደማለት ነው። ልፋቱን ተመልክቶ ካሰው እንደማለትም ነው። ስራ ለሰሪው እሾህ ለአጣሪው እንደተባለው እኩይ ስራን በሌላው ላይ የሚስራ ሁሉ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ይመለስለታል። ሰዎችን መበደል ወደፊት እኛን ለሚበድሉ ሰዎች አሳልፎ ይሰጠናል። ሰዎችን መዋሽት የሚዋሹ ሰዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፤ ሰዎችን መስረቅ በተለያዩ ምክንያቶች የእኛም ንብረት እንዲሰረቅ ይሆናል። ለሰዎች ጥሩ ባልተመኘን ቁጥር ለእኛ መጥፎ የሚስቡና የሚመኙ ሰዎች ይፈጥራሉ። በሰዎች ላይ በውሸት መፍረድ ያስፈርድብናል። በአንፃሩ ደግሞ ለሰዎች ጥሩ ማድረግ ወደፊት ጥሩ እንዲደረግልን ያደርጋል። ለለዎች ስንታመን ሰዎችም ለእኛ ይታመኑልናል። ለለዎች እውነታንና ግልፅነትን የምናንፀባርቅ ከሆነ እንዲሁ ሰዎችም ለእኛ እንዲሁ ይሆኑልናል። ለሰዎች ጥሩ ስንመኝ ለእኛ ስኬት የሚመኙ ሰዎች ይበዙልናል። ሰዎችን ለስኬት እንዲደርስ ስናግዛቸው ለስኬታችን የሚያግዙ ሰዎችን እናገኛለን። ሰዎችን ስናፈቅርም እንዲሁ የሚያፈቅሩን ሰዎች ይፈጠራሉ።
እንደሚታወቀው ሁለት አይነት ሀይል አለ፤ ሃሳባዊ ሀይልና ድርጊታዊ ሀይል። ሃሳባዊው ሀይል በአዕምሯችን ውስጥ የሚከወንና ከውስጣችንም በመውጣት ወደ ውጭ በመሰራጨት በሌሎች ሰዎች አዕምሮ ውስጥም ተፅዕኖን የመፍጠር ሀይል ያለው ነው። ይህ መሰል አዕምሯዊ የአስተሳሰብ ሀይል በሌሎች ሰዎች ላይ ሳይቀር ተፅዕኖን እንደሚፈጥር በሳይንሳዊ ጥናት ተረጋግጧል
ሌላው ደግሞ ድርጊታዊ ሀይል ነው:፡ ይህ ሀይል በአካላችን በኩል የሚንፀባረቅ ወይም ደግሞ በንግግራችን በኩል የሚገለፅ ሊሆን ይችላል. ሁለቱም ሀይሎች በሌሎች ሰዎች ላይ ተፅዕኖን የሚያሳርፉ በመሆናቸው ወደ እኛም ተመጣጣኝ ምላሽን ይዘው ነው የሚመጡት: በመሆኑም ስለሰዎች ስናወራ ስለ አሉታዊ እነሱነታቸው ሳይሆን ስለ አዎንታዊ ባህሪያቸውና ስራቸው ቢሆን ሌሎች ሰዎችም ስለ እኛ ገንቢና አዎንታዊ ማንነት ይናገራሉ: በአንፃሩ ደግሞ አሉታዊ በሆነ መልኩ የምናማቸው hሆነ እንዲህ መሰል ለዎችን በእኛ ላይ እንዲፈጠሩ እናደርጋለን፡፡ በድርጊት በኩልም የሚገለፀው ሀይል ይህንኑ ያንፀባርቃል፡ ለየትኛውም አይነት ነገር፣ ፍጡር፣ ሰው፣ በተቻለን አቅምና አጋጣሚ ውስጥ የምንችለውን በጐ ነገር ማድረግ ከዕለታት አንድ ቀን ባልጠበቅነው ቦታና አጋጣሚ ካልጠበቅነው ሰው ወይም ፍጡር ወይም የትኛውም ነገር የበለጠ ተደርጎ ይከፈለናል፡ ይህ የዩኒቨርሳችን የምንጊዜም ህግ ነው፡
ከሰዎች ፍቅር የምትፈልግ ከሆነ በቅድሚያ ፍቅርን ስጥ፣ ሰዎች እንዲያዳምጡህ የምትፈልግ ከሆነ በቅድሚያ አዳምጣቸው፣ ሰዎች በመንገድ ላይ በነፃነት እንዲያሳልፉህ የምትፈልግ ከሆነ በቅድሚያ አንተ አሳልፋቸው፣ ከሰዎች ገንዘብ የምትፈልግ ከሆነ በቅድሚያ ገንዘብ የሚፈጥር አንዳች ነገር አበርክትላቸው ሰዎች ኑሮህን እንዲያሻሽሉልህ የምትሻ ከሆነ የእነሱን ኑሮ በማሻሻል ትጋ፣ ፍቅረኛህ ለአንተ ታማኝ ትሆን ዘንድ አንተ መታመንን በተግባር አሳያት፣ እውነተኛ ስዎችን የምትፈልግ ከሆነ እውነተን ግልፅነትን ቀድመህ በተግባር አሳያቸው።
በድርጊት ብቻ ሳይሆን በሃሳብህም ጭምር ተፅዕኖ ማሳደር ትችላለህ። በአንድ ወቅት በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ በዓለም ላይ ታዋቂ የሆኑ የሜዲቴሽን ባለሙያዎች ለተከታታይ ወራት በውስጣቸው ሰላምን የሚሰብክ አስተሳሰባቸው የሜዲቴሽን ትግበራን መፈፀማቸው አይነጋም። በዚህም ሀይላቸ የተነሳ በዋሽንግተን ውስጥ የሰላም መጠን በጣም መጨመሩን የከተማዋ የደህንነት ማዕከል ከባለሙያዎቹ ጋር አረጋግጣል። እንደሚታወቀው ዋሽንግተን በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የግድያ ወንጀል ከሚፈፅሙባት ከተሞች ውስጥ ግንባር ቀደም ነች። ይሁን እንጂ የሚዲቴሽን ባለሙያዎቹ የሰላም ሞገድን ለተከታታይ ቀናት በመልቀቃቸ የተነሳ ባደረጉት ሃሳባዊ ተፅዕኖ በወቅቱ የግድያ ወንጀል በ25 በመቶ መቀነሱ ተዘግቧል።
በእርግጥ ሃሳባዊ ተፅዕኖ ምን ያህል ሀይል እንዳለውም መጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር የገለፀ ጉዳይ ነው። አንዱ ለአንዱ መፀለይ ምን ያህልም ውጤታማ እንደሆነ ይገልፃል። በመሆኑም በሀሳባችን ሳይቀር ለሰዎች ጥሩ የምንመኝ ከሆነ ይሄው ሀይል ወደ እኛ ገንቢ የሆነ ነገርን ይዞ ይመለሳል። በአንፃሩ ደግሞ በሃሳባችንም ሆነ ስሜታችን ለሌሎች መጥፎ የምናስብና የእነሱን ወድቀት የምንመኝ ከሆነ ይሄው የተፈጥሮ ህግ ወደ እኛ አባዝቶ የሚመልሰው።
የትኛውም ሰው የሚያጭደው የዘራውን ነው። ስንዴ ዘርቶ እንክርዳድ ወይም ደግሞ በቆሎን ያጨደ የለም። ትንሽ ጤፍ ዘርቶ ብዙ ጤፍን እንጅ አሜኬላን ያጨደ የለም። በአንፃሩ ደግሞ እንክርዳድ ዘርቶም የካናዳ ስንዴን የመሰለ ምርጥ ዘር ማጨድ አይቻልም። ሁለት እጆች ያሉን በሁለቱም ለመቀበል ሳይሆን በአንዱ በመስጠት በሌላኛው ለመቀበል ነው። ሁለት ጆሮዎች ያሉን በአንዱ ለማዳመጥ በሌላው ለማስደመጥ ነው። አንድ ምላስ ያለን ሌላም ምላስ ያለው ተናጋሪ ስላለ ነው። በዚህ ህግ መሰረት ከስዎች የምትፈልገውን የትኛውም ነገር ቀድመህ በመስጠት ከስዎች ብዙ ታገኛለህ። ይሁን እንጅ በተራህ ከእነርሱ የምትጠብቀውን ልዩ ልዩ ነገር ያላገኘህ ከሆነ ደግሞ ቀድመህ ላለመስጠትህ ምላሽ መሆኑንም መረዳት አለብህ። ሰላልዘራህ አላጨድክም። አራት ነጥብ!
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
አልፋና ኦሜጋ ቁጥር ፩ - ገጽ 22-24
Comments
Post a Comment