Posts

የቻይና 1 ኪሜ የሚረዝመው የህዋ ላይ መጓጓዣ ግንባታ

በተለያዩ የሆሊውድ ሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልሞች ላይ እጅግ ግዙፍ የሆኑ የህዋ ላይ መጓጓዣ ወይም ስፔስሺፖችን አይተናል፡፡ ታድያ እነዚህን ግዙፍ የህዋ ላይ መጓጓዣዎች ከፊልምም ባሻገር እውን እንዲሆኑ የሚያስችል እንቅስቃሴ በቻይና ተጀምሯል፡፡ ሀገሪቱ 1 ኪ.ሜ የሚረዝም የህዋ ላይ መጓጓዣን መስራት ስለሚቻልበት መንገድ ጥናት ጀምራለች። ስራውን አስመልክቶ ይፋ የተደረገው ጽሑፍ እንዳመላከተው ይህ ግዙፍ የህዋ ላይ መጓጓዣ ወደፊት የህዋ ሀብትን ለመጠቀም፣ ድብቁን የዩኒቨርስ ከባቢ ለማሰስ እንዲሁም ረዘም ላለ ጊዜ ለመኖር የሚያገለግል ነው፡፡ አሁን ላይ መጓጓዣውን አስመልክቶ 2.3 ሚሊዮን ዶላር የሚያስወጣ የአዋጭነት ጥናት ለማከናወን ሲታቀድ ተመራማሪዎችም ወደ ህዋ ተልኮ ለግንባታው የሚውለውን ግብዓት በሚቀንስ መልኩ ቀለል ያለ ንድፍ እንዲሰሩ ይፈለጋል፡፡ ግን ይቻላል? ይህን የሚያክል የህዋ ላይ መጓጓዣ መስራቱ በሳይንሳዊ ልብ ወለድ ፊልሞች ላይ ብቻ የሚሳካ ነገር ቢመስልም የዘርፉ ተመራማሪዎች ግን ከሳይንስ አንፃር እንዳይሳካ የሚያደርግ ተግዳሮት እንደሌለው ይገልፃሉ፡፡ ሆኖም በእንዲህ አይነት ግንባታ ላይ አንዱ ተግዳሮት ከስራው ግዝፈት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የምህንድስና ስራ ነው፡፡ ሌላውና ትልቁ ተግዳሮት ግን የወጪው ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም የግንባታ ቁሳቁሰሶችን ወደ ህዋ ማጓጓዙ ሲበዛ ውድ ነው፡፡ ለምሳሌ ወደ ጎን 110 ሜትር የሚረዝመው ዓለም አቀፉ የህዋ ምርምር ጣብያን (ISS) ለመገንባት 100 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል፡፡ አዲሱ እቅድ ከዚህ 10 እጥፍ የሚረዝም አካል መገንባት መሆኑን ከግምት ስናስገባ ወጪውን ጭንቅላት የሚያዞር ያደርገዋል፡፡ የህዋ ላይ ማጓጓዣው ሰዎችን እንዲይዝ ተደርጎ የሚሰራ ከሆነ ደግሞ ወጪውን ይባስ ያንረዋል፡፡ ነገር ግን ወጪው በዋናነት የህዋ

“ሜሲን የምትበልጠው” ሮቦት ተጫዋች

የቻይናዋ ሮቦት ዜና አንባቢ

“ከሞቱ ሰዎች ጋር መነጋገር” የሚያስችለው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

ድምጽን በመስማት ብቻ ጉንፋንን የሚለየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

በፎቶ እድሜ የሚናገረው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በ10 ዓመት ውስጥ ከሰው ልጅ የማሰብ አቅም በላይ እንደሚሆን ተገለጸ

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ህይወት እንዴት እያቀለለ ነው?

ቢትኮይን - ክፍል ፩ - የቢትኮይን መወለድ

ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሰው ልጆች መጥፊያ ይሆናል?

ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የማይወስዳቸው ሥራዎች አሉ?

ሥራችንን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ልንነጠቅ እንችላለን?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመውን “የሲስተም ችግር”

አሜሪካ እና ቲክቶክ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ሊነሳ ጫፍ ላይ መድረሱን ተናገሩ

በሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቭላድሚር ፑቲን በከፍተኛ ድምጽ አሸነፉ

በበርካታ የአፍሪካ አገራት የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

ሊንዊ ዲንግ - የጎግልን ቁልፍ ሚስጥሮች ለቻይና ሲያስተላልፍ የነበረውን ባለሙያ

ጥቁር መረብ (Dark web)