ጥቁር መረብ (Dark web)
⚠️ Only for education purpose⚠️
👉 ጥቁር መረብ የጥልቅ መረብ (Deep web) ትንሹ አካል ሲሆን ከሌላው መረብ (Standard Web) የተደበቀ ነው። Dark web በተለመዱት Browser ሶፍትዌሮች (Opera, Firefox, Chrome) መገኘት አይችልም። Dark web በህግ የተከለከሉ እቃዎች የሚሸጡበት እና ከፍተኛ የሆነ የጥቁር ገበያ (Black Market) የሚካሄድበት ቦታ ነው። በDark web ውስጥ እንደ ናርኮቲክ፣ የልጅ ወሲብ ፊልሞች፣ የተሰረቁ ክሬዲት ካርዶች እና ሌሎች ህገ-ወጥ እቃዎች በቀላሉ ይገኛሉ። በDark web ውስጥ ግብይቶች በቢትኮይን (Bitcoin) እና በሌሎች የኤሌክትሮ ሜል መገበያያ መንገዶች ይከናወናሉ።
👉 Dark web ሁለት አይነት ኔትወርክ ይጠቀማል። አንደኛው አቻ-ለ-አቻ-ኔትወርክ (peer to peer network) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ታዋቂ አውታረ መረቦች ያሉ ቶር (Tor)፣ ፍሪኔት (Freenet)፣ አይቱፒ (I2P)፣ ሪፍል (Riffle) እንዲሁም በህዝባዊ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የሚተዳደሩ ኔትወርኮችን ያካትታል። የጨለማው ድር ተጠቃሚዎች መደበኛ ድርን (standard web) የማይጠቅሙበትን ምክንያት ሲናገሩ " ሚስጥራዊ ባለመሆኑ ምክንያት ማንም ሰው ሊያጠቃን ወይም መረጃ ልንተውለት እንችለን" ብለው ያምናሉ።
👉 ጨለማ ድር ከሚያስጠቅም ሶፍትዌር መካከል ዋናው እና ታዋቂው ቶር ብሮዘር (Tor Browser) ነው። ቶር ብሮዘር ኦውየንላንድ በመባል የሚታወቀው የኔትወርክ ከፍተኛ ደረጃን (top domain) ቅጥያ (suffix) የሚጠቀም ሲሆን ከፍተኛ የሆነ መመስጠሪያ ስልተ ቀመር (encryption algorithm) ይጠቀማል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚውን ለማግኘት ወይም ጠለፋ (hacking) ለማድረስ የተወሳሰበ ያረገዋል።
በጥቁር ድር ያሉ አገልግሎቶች
☠️ ቦትኔት (botnet)
☠️ የቢትኮይን አገልግሎቶች
☠️ የጥቁር ገበያ
☠️ የጠለፋ አገልግሎቶች (hacking Service)
☠️ የማጭበርበር አገልግሎቶች
☠️ ሽብርተኝነት (terrorism)
☠️ አደገኛ እፅ እና ሌሌችም
Comments
Post a Comment