ቢትኮይን የተወለደው እ.ኤ.አ. በ2008 አ.ም አካባቢ ነው። አንድ ቀን ሳቶሺ ናካሞቶ (Satoshi Nakamoto) በሚባል ስም የሚጠራ ግለሰብ ወይም ቡድን "Bitcoin: A Peer-to-Peer Electronic Cash System" የሚል ነጭ ወረቀት ድረ ገፅ ላይ አስቀመጠ። ይህም ወረቀት እንደ ባንክ ያለ ማዕከላዊ ባለሥልጣን ሳያስፈልግ ሊሠራ የሚችል ያልተማከለ ዲጂታል ምንዛሪ ጽንሰ-ሐሳብን ይዘረዝራል።
ጥናታዊ ጽሑፉን በPDF ለማውረድ ይህንን ይጫኑ።
ይህ ነጭ ወረቀት ለቢትኮይን መፈጠር አጋዥ የሆኑ በርካታ ቁልፍ ፅንሰ ሀሳቦችን አስተዋውቋል። ግብይቶችን ለማስጠበቅ እና አዲስ የመገበያያ ሚንዛሬዎችን ለመፍጠር ክሪፕቶግራፊክ ቴክኒኮችን በመጠቀም ሀሳብ በማቅረብ ያለማዕከላዊ ባለስልጣን በአውታረ መረብ ተሳታፊዎች መካከል ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ዘዴን ዘርዝሯል።
ሳቶሺ ናካሞቶ እ.ኤ.አ. በ2009 አ.ም እንደ ክፍት ምንጭ ሶፍትዌር የተለቀቀውን የቢትኮይን ሶፍትዌር የመጀመሪያ አተገባበር አዘጋጅቷል። ይህ ሶፍትዌር ተጠቃሚዎች ኮምፒውተርን በማስኬድ በቢትኮይን አውታረመረብ ውስጥ እንዲሳተፉ አስችሏቸዋል። ይህም በኔትወርኩ ላይ ግብይቶችን ለማረጋገጥ እና ለማሰራጨት ይረዳል።
የቢትኮይን ጅማሬ የማወቅ ጉጉት፣ ጥርጣሬ እና ደስታን በማጣመር በማህበረሰቡ ዘንድ ፈጥሮ ነበር። ብዙ ሰዎች ከመንግሥታት እና ከባህላዊ የፋይናንስ ተቋማት ቁጥጥር ውጭ ሊሰራ የሚችል ያልተማከለ ዲጂታል ምንዛሪ አቅም ግርምት አድሮባቸው ነበር። ሌሎች ደግሞ ስላለው እውነተኛ ዋጋ ጥርጣሬ እና ለህገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ሰለመዋሉ ስጋት እና ፍራቻ ውጧቸው ነበር።
በመጀመሪያዎቹ የቢትኮይን የእድገት ጊዚያት እምቅ ችሎታውን ያዩ እና አዲሱን ቴክኖሎጂ ለመሞከር ፈቃደኛ የሆኑ ትንሽ ነገር ግን ቁርጠኛ የሆነ የተጠቃሚዎች ነበሩ። ሆኖም ግን ቢትኮይን አሁን ወዳለበት ሰፋ ያለ እውቅና ከማግኘቱ እና የበለጠ ትኩረትን ከመሳብ በፊት የተወሰነ ጊዜ ወስዷል።
በቢትኮይን የመጀመሪያ ታሪክ ውስጥ ካሉት ቁልፍ ክንውኖች አንዱ ቢትኮይን በመጠቀም የተደረገው የመጀመሪያው የገሃዱ ዓለም ግብይት ነው። እ.ኤ.አ. በግንቦት 2010 አ.ም ላስዝሎ ሀንዬክዝ (Laszlo Hanyecz) የተባለ ተጠቃሚ ሁለት የፓፓ ጆን ፒዛዎችን በ10,000 BTC ገዛ። ይህ ግብይት አሁን እንደ የቢትኮይን ፒዛ ቀን የሚከበር ሲሆን ቢትኮይን ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ ምን ያህል ርቀት ላይ እንደደረሰ የሚያስታውስ ነው።ባለፉት አመታት ውስጥ ቢትኮይን እውቅናው እየሰፋ፣ እያደገ እና በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑ ክሪፕቶከረንሲ ምንዛሬዎች አንዱ እና ቀዳሚ ሆኗል። ያልተማከለ ተፈጥሮው እና አቅርቦት ውሱንነት እንደ አማራጭ የሀብት ማከማቻ እና ከባህላዊ የፋይናንሺያል ስርዓቶች ሀብትን የሚጠብቅ አጥር እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል።
የቢትኮይን መወለድ ለጠቅላላው የክሪፕቶ ምንዛሬ ወይም ክሪፕቶከረንሲ እና የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ምህዳር እድገት መንገድ ከፍቷል። ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ክሪፕቶ ምንዛሬዎች ሲኖሩ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ልዩ ባህሪያት እና የአገልግሎቶች አሏቸው።
በክፍል ፪ - ይቀጥላል!
Bitፍራንክ - የዲጂታል ገንዘብ የወደፊት ዕጣ - ገጽ 6 - 8
Comments
Post a Comment