ስቲቨን ሃውኪንግ - አጭር ታሪክ

ስቲቨን ሃውኪንግ

    በዕለተ ረቡዕ መጋቢት 10 2010 ዓመተ ምህረት ሳይንስ ታላቅ ባለውታዋን ሸኘች፡፡ የዘዋርድ ፕሮፌሰር ሰቲቨን ሃውኪንግ በ76 ዓመቱ ከዚህች ዓለም በሞት ተለየ ተለይቷል፡፡ ስቲቨን ሃውኪንግ ገና በለጋ እድሜው ALS በተሰኘው በሽታ የተጠቃ እና ሙሉ ህይወቱን ያለ እንቅስቃሴ እንዲሳልፍ የተገደደ ቢሆንም ከበሽታው በላይ በመሆን ለዓለም አለሁልሽ ብሏታል፡፡

    ስቲቭን በጃንዋሪ 8፤ 1942 ዓመተ ምህረት (ልክ ጋሊሊዮ በሞተ በ300 ዓመቱ) በእንግሊዝ በኦክስፎርድ ከተማ ተወለደ፡፡ ይህ ታላቅ ሰው ለሳይንስ የታጨው ከመወለዱ በፊት ይመስላል፡፡ አባቱ ፈራነንከ ሃውኪንግ ባዮሎጂስት የነበረ ሲሆን እናቱ ኢዛቤል ደግሞ የህክምና ምርምር ተቋም ሰራተኛ ነበረች፡፡ በ1959 በ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ስኮላር በማግኘት በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ለማግኘት ችሏል፡፡

    በሳይንስ ውስጥ ልዩ ጠዓምን እያገኘ የመጣው ይህ ታላቅ ሳይንቲስት በ1962 ዓመተ ምህረት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲበ Department of Applied Mathematics and Theoretical Physics (DAMTP) የኮስሞሎጂ ምርምር ስራዎችን ማከናወን ጀመረ፡፡

    ይሁንና በ1963 ልክ የ21 ዓመቱን ልደት እንዳከበረ ከባድ ነገር አጋጠው፤ እድሜውን በሙሉ በወንበር ላይ እንዲታሰር ሆነ፡፡ ይህ በሽታ እንቅስቃሴውን ብቻ አልነበረም የቀማው ድምፁንም ጨምሮ ቢሆን እንጂ፡፡ ሰቴቭን የኮምፑተር ጥገኛ ሆነ፡፡ የስቲቭን ጉዞ ግን በዚህ አላበቃም ጅማሬው ቢሆን እንጂ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም በ1965 ዓ.ም Properties of Expanding Universes በሚለው የምርምር ውጤቱ ምክንያት የPhD ማዕረጉን ሊያገን ቻለ፡፡

    ስቲቭን 30 የሚሆኑ የክብር ዲግሪዎችን ያገኘ ሰው ሲሆን በርካታ ሽልማቶችንም ተጎናፅፏል፡፡ ስቲቭን በአልበርት አንስታይን የተጀመሩ ስራዎችን ያስቀጠለ እና በተለይም በRelativity እና በQuantum theory ውስጥ ጥልቅ አሻራን ያስቀመጠ ሰው ነው፡፡

    ፕሮፌሰር ሰቴቭን የ3 ልጆች አባት እና የ 3 ልጆች አያት ነው፡፡ ስቴቭን በ2010 ዓ.ም ለABC's "World New Tonight," በሰጠው ቃለ ምልልስ ወቅትም ለልጆችህ ሰጥተኸው የምታውቀው ምርጥ ምክር ምንድ ነው በተባለ ሰዓትም እንዲህ ብሎ መልሷል፡፡

"ለልጆቼ የሰጠኋቸው 3 ምርጥ ምክሮች አሉ እነርሱም፦

        1ኛ፦ ሁሌም ቢሆን ወደ እግራችሁ ታች እየተመለከታችሁ ወደ ላይ ወደ ኮከቧማንጋጠጥን አትርሱ፡፡

        2ኛ፦ ሁሌም በስራ ላይ ሁኑ፡፡ ስራ ለህይወታችሁ ምክኒያት እና ለመኖራችሁ ዓላማን ያጎናፅፋችኋል፡፡

        3ኛ፦ እድለኛ ሁናችሁ ፍቅርን በህይወታችሁ ውስጥ ልታገኙ ከቻላሁ በጣም የማይገኝ ዕድል ነውና በቀላሉ አትልቀቁት፡፡

ዓለም እንዲህ ያሉ ሰዎችን በቀላሉ የምትለግስ ባትሆንም ሁሌም ግን ህልፈታቸውን የሚተካ ሳታዘጋጅ አልፋ አታውቅም፡፡

A Brief History of Time እና The Universe in a Nutshell የሚሉትን የእርሱን 2 ምርጥ መፅሀፎች ተጋበዙልን እንላለን፡፡


ምንጭ ፡- BBC News

ቴሌግራም ላይ Join ያድርጉ

Comments