በቤርሙዳ ትራያንግል ላይ የጠፉ መርክቦች ዝርዝር በትንሹ

 

በቤርሙዳ ትራያንግል ላይ የጠፉ መርክቦች ዝርዝር በትንሹ

    ቤርሙዳ ትራያንግል ምንም መረጃ ሳያገኙ በተሰወሩ መርከቦች፣ አውሮፕላኖችና ሰዎች ምክንያት ለብዙ ዓመታት የሰዎችን ሓሳብ ሰርቆ የያዘና እስከ ዛሬ ድረስ ማብራሪያ ካልተገኘላቸው የምድራችን ምስጢራዊ ቦታዎች አንዱ ነው። 

🚢 በ1800 ዩ.ኤስ.ኤስ ፒክሪንግ (USS Pickering) የተባለች የአሜሪካ ባሕር ኀይል መርከብ 90 ሰዎችን አሳፍራ ከግዋድሉፕ (Guadeloupe) ወደ ዴልዌር (Delaware) እየተጓዘች ደብዛዋ ጠፍቷል።

🚢 በ1814 ዩ.ኤስ.ኤስ ዋስፕ የተባለች መርከብ 140 ሰዎችን አሳፍራ እየተጓዘች ካሪብያን አካባቢ ተሰወረች።

🚢 በ1824 ዩ.ኤስ.ኤስ ዋይልድ ካት የተባለች መርከብ 14 ሰዎችን ጭና ከኩባ ወደ ቶምኪንስ ደሴት እየተጓዘች ጠፍታለች።

🚢 በ1840 ሮዝሊ (Rosalie) የተባለች መርከብ የጫነቻቸው ሰዎች ጠፍተው ብቻዋን ስትንሳፈፍ ተገኝታለች።

🚢 በ1880 አትላንታ የተባለች መርከብ 290 ሰዎችን ጭና ከቤርሙዳ ወደ እንግሊዝ እያቀናች ከቤርሙዳ ብዙም ሳትርቅ ከነሰዎቿ የገባችበት ጠፋ።

🚢 በ1918 ዩ.ኤስ.ኤስ ሳይክሎፕስ የተባለች ግዙፍ መርከብ 309 ስዎች ጭና ከባርባዶስ (Barbados) ወደ ባልቲሞር (Baltimore) እየተጓዘች ከነሰዎቿ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታለች። በወቅቱ የአየሩ ሁኔታ ጥሩ እንደነበርና የሬድዮ መልእክትም እንዳስተላለፈች የተዘገበ ሲሆን መርከቧን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ምንም ፍንጭ ሳይገኝበት ተጠናቋል።

🚢 በ1912 ካሮል ዲሪንግ (Carroll Deering) የተባለች መርከብ የጫነቻቸው ሰዎች የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ብቻዋን ሰሜን ካሮላይና ተንሳፋ ተገኘች።

🚢 በ1925 ኤስ.ኤስ ኮቶፓክሲ (SS Cotopaxi) የተባለች መርከብ ከቻርልስተን (Charleston) ተነሥታ ወደ ሀቫና ኪውባ (Havana, Cuba) 32 ሰዎችን ጭና እየተጓዘች ጠፍታለች። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚገርመው ነገር በ2020 ላይ መርከቧ ከጠፋች ከ95 ዓመት በኋላ የመርከቧ ስብርባሪ ከፍሎሪዳ የባሕር ዳርቻ ላይ በሚገኘው የባሕር ወለል ላይ መገኘቱ ይፋ ተደርጓል።

🚢  በ1963 የካቲት 2 “ማሪን ሰልፈር ኩዊን” (Marine Sulphur Queen) የተባለች ድኝ (Sulphur) የተባለ ማእድን እና 39 ሰዎች ጭና ስትጓዝ የነበረች መርከብ ከነሰዎቿ ስብርባሪዋ እንኳን ሳይታይ ደብዛዋ ጠፍቶ ቀረ።

🚢 በ2015 ሐምሌ 24 ሁለት የ14 ዓመት ልጆች በባሃማ ዓሣ የማጥመድ ጉዞ ብለው ወጥተው ሳይመለሱ ደብዛቸው ጠፋ። የአሜሪካ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ብዙ ቦታ የሸፈነ ፍለጋ ቢያደርጉም ሊገኙ አልቻሉም። ጀልባዋ ግን በዓመቷ ቤርሙዳ ጠረፍ ላይ የተገኘች ቢሆንም ልጆቹ ግን በዛው ጠፍተው ቀርተዋል።

🚢 በ2015 ጥቅምት 1 ኤስ.ኤስ ኢ.ኤል ፋሮ (SS El Faro) የተባለች መርከብ 33 ሰዎችን ጭና ከፍሎሪዳ ወደ ፑርቶሪኮ እየሄደች ሳለች ቤርሙዳ ውስጥ ባሃማስ ጠረፍ አካባቢ መስመጧ ሲነገር ተርፎ የተገኘ ሰውም አልነበረም።

ምንጭ፦ አንድሮሜዳ ቁጥር 2 ገጽ 311-312

ቴሌግራም ላይ Join ያድርጉ

Comments