በቤርሙዳ ትራያንግል ላይ የጠፉ አውሮፕላኖች ዝርዝር በትንሹ

በቤርሙዳ ትራያንግል ላይ የጠፉ አውሮፕላኖች ዝርዝር በትንሹ

በዛሬው ጡማር “በቤርሙዳ ትራያንግል ላይ የጠፉ አውሮፕላኖች ዝርዝር በትንሹ” በሚል ርእስ በቤርሙዳ ትራያንግል አካባቢ የተሰወሩ አውሮፕላኖች ዝርዝር ልናካፍላችሁ ወደድን

✈️ በታኅሣሥ 5 1945 ቲ.ቢ.ኤም አቬንጀርስ (TBM Avengers) የተባሉ እና በበረራ ቁጥር 19 የሚታወቁ 5 የአሜሪካ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ከፍሎሪዳ ፎርት ሎደርዴል (Florid, Fort Lauderdale) ለበረራ ልምምድ ወጥተው ከሁለት ሰዓታት ቆይታ በኋላ ደብዛቸው ጠፋ። አምስት አብራሪ መኮንኖችና ዘጠኝ ረዳቶቻቸው በአጠቃላይ 14 የባሕር ኀይሉ አባላት ነበሩበት። የበለጠ በጣም የሚገርመው ደግሞ በዛ ዕለት እነዚህን አውሮፕላኖች ለመፈለግ ሄዶ የነበረው ፒ.ቢ.ኤም ማርቲን ማሪነር (PBM Martin Mariner) የተባለውም አውሮፕላንም 13 ሰዎችን እንደ ጫነ በዚያው የውሃ ሽታ ሆኖ ደብዛው መጥፋቱ ነበር።

✈️ በሐምሌ 3 1947 ሲ-54 (C-54) የሚባል የአሜሪካ ጦር ሰራዊት አውሮፕላን 7 ሰዎችን ጭሮ ከቤርሙዳ ወደ ማያሚ እየበረረ እያለ ከቤርሙዳ 100 ማይልስ ርቀት ላይ መጥፋቱ ተነገረ።

✈️ በታኅሣሥ 28 1948 ዲሲ-3 (DC-3) የተባለ የመንገድኞች አውሮፕላን 31 ሰዎችን ጭኞ ከሳን ህዋን (San Juan) ወደ ማያሚ (Miami) እየበረረ ሳለ ከሚያሚ ሰሜናዊ አቅጣጫ አካባቢ መሰወሩ ተነገረ።

✈️ በጥር 17 1949 ስታር ኤሪያል (Star Ariel) የተባለ አውሮፕላን 7 አውሮፕላኑ ሠራተኞችን እና 13 መንገደኞችን ጭኖ ከቤርሙዳ ወደ ኪንግስተን (Kingston) እየበረረ ከቤርሙዳ ደቡብ ምስራቅ 300 ማይልስ ላይ የሬድዮ ግንኙነቱ ተቋረጠ አውሮፕላኑም ደብዛው ጠፋ።

✈️ በጥቅምት 30 1954 ሱፐር ኮንስትሌሽን የተባለ የአሜሪካ የባሕር ኃይል አውሮፕላን 42 ሰዎችን ጭኖ ከሜሪላንድ (Maryland) ወደ አዞርስ (Azores) እየበረረ ከቤርሙዳ በስተሰሜን ሲደርስ ድምፁ ጠፋ ። ከተሰወረ ጥቂት ጊዜ በኋላ በደንብ ያልተሰማ የአደጋ ጊዜ ጥሪ መተላለፍ ጀምሮ ነበር፤ ነገር ግን ወዲያኑ ጠፋ።

✈️ በጥር 8 1962 ኬ.ቢ.50 (KB-50) የተባለ የአሜሪካ አየር ኃይል አውሮፕላን 8 ሰዎችን ጭኖ ከሰሜናዊ ካሮላይና ወደ አዞርስ እየበረረ ሳለ በአሜሪካና አዞርስ መሃል ላይ ጠፋ።

✈️ በነሐሴ 28 1963 ኬ.ሲ.135 የተባሉ ሁለት አውሮፕላኖች 10 ሰዎች ይዘው ወጥተው በሰላም ወደነበሩበት እየተመለሱ መሆናቸውን ተናግረው ከዛ ድምፃቸው ጠፋ።

✈️ በመስከረም 22 1963 ሲ-133 ካርጎ ማስተር የተባለ አውሮፕላን 10 ሰዎችን እንደ ጫነ ወደ አዞርስ እየተጓዘ እያለ ጠፋ።

✈️ በሠኔ 9 1965 ሲ-199 የተባለ አውሮፕላን 10 ሰዎችን ጭኖ ከሚያሚ ወደ ግራንድ ተርክ (Grand Turk) እየበረረ ሳለ በፍሎሪዳ ናግራንድ ተርክ ደሴት መሃል ድራሹ ጠፋ።

✈️ ጥር 11 1967 ቼዝ.ዋይ.ሲ 122 (Chase YC-122) የተባለ አውሮፕላን 4 ሰዎችን ጭኖ እየተጓዘ እያለ በፎርት ሎውደርዴል (Fort Lauderdale) እና ባሃማስ (Bahamas) መሃል ደብዛው ጠፋ።

✈️ ሚያዚያ 10 2007 10 ፓይፐር ፒኤ-46-310ፒ (Piper PA-46-310P) የተባለ አውሮፕላን ስብርባሪው እንኳን ሳይገኝ ጠፍቶ ቀረ።

✈️ ታኅሣሥ 15 2008 ቢኤን-ቱ. ኤ ትሪስላንደር (BN-2A trislander) የተባለ አውሮፕላን ከሳንቲያጎ ወደ ባሃማስ እየተጓዘ ካሪቢያን ባሕር አካባቢ ሲደርስ መጥፋቱ ተነገረ።

✈️ ግንቦት 15 2017 ኤምዩ 2ቢ (MU 2B) የተባለ አውሮፕላን ከፑርቶሪኮ ወደ ፍሎሪዳ እየተጓዘ ከራዳር ውጪ ሆነ። አውሮፕላኑም የውሃ ሽታ ሆነ።

ምንጭ፦ አንድሮሜዳ ቁጥር 2 ገጽ 321-316

ቴሌግራም ላይ Join ያድርጉ

Comments